Fana: At a Speed of Life!

ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል የ2030 የዓለም ዋንጫን እንደሚያዘጋጁ ፊፋ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል በ2030 የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ በጋራ እንደሚያዘጋጁ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር የበላይ ጠባቂ (ፊፋ) አስታውቋል፡፡

በውድድሩ መክፈቻ የሚደረጉ ሦስት ጨዋታዎች በኡራጓይ፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ እንደሚካሄዱም ነው ፊፋ ያስታወቀው፡፡

የመክፈቻ ጨዋታዎችን በላቲን አሜሪካ ሀገራት ለማድረግ የተወሰነው የዓለም ዋንጫ የሐገራት ውድድርን 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ታሳቢ በማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ውድድሩን የሚያዘጋጁት ስድስት ሀገራት ያለማጣሪያ  በቀጥታ ለውድድሩ እንደሚያልፉም ነው የተገለጸው፡፡

በ2030 የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በላቲን አሜሪካ አህጉራት በጋራ የሚደረግ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ እንደሚሆን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.