Fana: At a Speed of Life!

የህገ መንግስት ትርጉምን የተመለከተው የባለሙያዎች ሀሳብ መስጫ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የህገ መንግስት ትርጉምን በተመለከተ ያዘጋጀው የባለሙያዎች ሀሳብ መስጫ መድረክ በሸራተን አዲስ ተካሄደ።

ጉባኤው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረበለት ጥያቄ የሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለሙያዎች አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም በዛሬው ዕለት ከህገ መንግስት ትርጓሜና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ባለሙያዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በሃሳብ መስጫ መድረኩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ከህገ መንግስት ትርጓሜ ጋር በተያያዘ ባለሙያዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀረቡት ሃሳብና ማብራሪያዎች ላይ ጥያቄዎችን አቅርበው ከባለሙያዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.