Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ህዝባዊነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ባሻገር አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ህዝባዊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስቴር የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተመሰረተበትን 116ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩና ለአቅመ ደካሞች ከ103 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን ቤቶች አስረክቧል።

ቤቶቹ ከመኖሪያነት ባሻገር ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችንም ያካተቱ እንደሆኑም ነው የተነገረው።

በርክክብ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ ሠራዊቱ በሚኖርበት አካባቢ የሚገኙ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩና የአቅመ ደካሞችን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ ነው።

ሠራዊቱ ባለፉት ዓመታትም ቤቶችን በማደስ ሲያስረክብ መቆየቱን አንስተው፥ አሁን ላይ ደግሞ ዘመናዊ ቤቶችን ገንብቶ ሕዝብን የመደገፍ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

በዚህም ሠራዊቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ባሻገር ከደመወዙ በመቀነስ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልፀው፥ ደጀን ለሆነው ህዝብ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትሩ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም በችግር ውስጥ የነበሩ 16 አባዎራዎች ሲኖሩባቸው የነበሩ ደሳሳ ቤቶችን አፍርሶ ደረጃቸውን የጠበቁ 64 ቤቶችን የያዙ ሁለት ህንፃዎችን በመገንባት ማስረከቡንም አስታውሰዋል።

ቤቶችን የተረከቡ ቤተሰቦች ሠራዊቱ ችግራቸውን በመረዳት ምቹ መኖሪያ ቤት በመገንባት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.