Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ዑመር ባሕር ማኔስ ከተመራው ከፍተኛ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ የድንበር ማካለል፣ የኢትዮ ሱዳን የኢኮኖሚ ትሥሥርን ማጠናከር፣ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ተጽዕኖ በጋራ መከላከልን ጨምሮ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም የሃገራቱን ኢኮኖሚ በጋራ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ዑመር ባሕር ማኔስ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።

በወቅቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውለታል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.