Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በየአመቱ እየጎለበተ፣ እያማረበትና እያበበ መጥቶ የሁሉም ኢትዮጵያውያን በአል ሆኖ በማየቴ ታላቅ ደስታ ፈጥሮብኛል – ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ህዝብ ባህል የሆነው ኢሬቻ በየአመቱ እየጎለበተ፣ እያማረበትና እያበበ መጥቶ የሁሉም ኢትዮጵያውያን በአል ሆኖ በማየቴ ታላቅ ደስታ ፈጥሮብኛል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው 5ኛው የኢሬቻ ፎረምና የኢሬቻ ዋዜማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፤ ”ኢሬቻ የወንድማማችነት እና የአንድነት አርማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጀው 5ኛው የኢሬቻ ፎረምና የኢሬቻ ዋዜማ ዝግጅት የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ሚንስትሮች፣ የተለያዩ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ ከተለያዩ አከባቢዎችና ከተሞች እንዲሁም ከውጭ አገር የመጡ እንግዶች በተገኙበት ስለ ኢሬቻ ምንነት፣ የህዝቦችን ወንድማማችነትና አንድነት በማጠናከር ረገድ ያለውን ፋይዳ በመወያየት ተማምረናል ብለዋል።
በተዘጋጀው መርሐ ግብርም ሆነ በሆራ ፊንፊኔ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ መላው የኦሮሞ ህዝብና በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን በሰላምና በደስታ እንዲያሳልፉ እየተሰራ ላለው ስራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና መላው የከተማዋ ህዝቦች ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢሬቻ በዓልን ለማክበር በመንገድ ላይ ላሉና ለመጡት የሀገሪቱ ብሔር ብሄረሰቦች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መልካም የኢሬቻ በዓል እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የኢሬቻን በዓል አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክትም ለኦሮሞው ኢሬቻ ሁሉም ነገር ነው ብለዋል።

ፈጣሪውን በማመስገኑ አብሮነቱንና አንድነቱን በማጠናከር ወደ ስኬት እንደሚመራው ገልጸዋል።

ለውጡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የባህልና የታሪክ ቦታዎች ግንባታ፣ የባህል ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ፍትህን ለማስመለስ፣ የጠፋ ታሪክን በማረም እና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ማካተት ላይ ትኩረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ጀማሮውን በጥብቅ ምርምር በማስቀመጥ በተግባር እናሳያለን ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሁሉም የኦሮሞ ባህል፣ ታሪክና ቅርስ የአለም የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆኑ እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል መሰናክሎችን አልፎ የኦሮሞን ክብር ለአለም አሳይቷል በማለት ገልጸው፤ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ፣ ብሄሮችና ብሄረሰቦች መልካም የኢሬቻ በዓል እንዲሆንም ተመኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.