Fana: At a Speed of Life!

ር/መ ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር) ለኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር  ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ለኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የኢሬቻ በዓል የአንድነትና የወንድማማችነት በዓል መሆኑን ጠቅሰው፥ በዓሉ ያለ እምነትና ብሄር ልዩነት በአንድ ላይ ፈጣሪ የሚለመንበትና የሚመሰገንበት መሆኑን አመላክተዋል።

ኢሬቻ በዋናነት የኦሮሞ ማህበረሰብ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታና የአንድነት በዓል መሆኑን አንስተው፥ በዚህም በዓል ፍቅራችን እንድደረጅ፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት አንድጸና መተባባርና መከባባር እንዲሰፍን እንዲሁም ብሄራዊነት እንዲጎለብት አሳስበዋል ።

ከታላቁ ገዳ ሥርዓት ኢሬቻ አንዱ ነዉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በሕዝቦች መካከል ይቅርታን፣ ፍቅርን፣ ሰላምና አንድነትን በማስረጽ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት አብሮነትንና አንድነትን የሚያፀና ትልቅ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

ኢሬቻ ሁሉም በአንድነት የሚያከብረው የምስጋና በዓል በመሆኑ ሁላችንም የበዓሉ እሴቶች በሚያዘው አኳኋን ማክበር አለብን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የኢሬቻ በዓል የቱሪዝም ዘርፉን በማጠናከር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያለው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን በዓል ማስተዋወቅ፣ መጠበቅና መንከባከብ እንዲሚገባ ጠቅሰዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ መስተዳድሩ በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.