Fana: At a Speed of Life!

“የኢሬቻ በዓል የሰላም ምልክት ነው” – አባ ገዳዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢሬቻ በዓል አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የሰላም ምልክት መሆኑን” አባገዳዎች ገለጹ፡፡

የኢሬቻ በዓል የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የምስጋና እና የወንድማማችነት ተምሳሌት መሆኑን ነው አባገዳዎቹ የገለጹት፡፡

በዓሉ በኦሮሞ ሕዝብ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ የሰላም ምልክት ነው ሲሉ አባገዳዎቹ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ጥላቻ የሚወገድበት፣ አንድነት የሚሰበክበት፣ መጪው ጊዜ ብሩኅ እንዲሆን ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ጸሎትና ምስጋና የሚደረግበት የወንድማማችንት መገለጫ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ኢሬቻ የኢትዮጵያውያንን የእርስ በርስ ትስስር የሚያጠናክር የአብሮነት መገለጫ ነው ብለዋል አባገዳዎቹ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.