Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በሁሉም የግብርና ልማት መስኮች ይሳተፋል- ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በግብርና ልማት ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በሁሉም የግብርና ልማት መስኮች ላይ የሚሳተፍ መሆኑን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ዐቢይ ኮሚቴ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የግብርናውን ሴክተር ራዕይ፣ ግቦችና የ10 አመቱን መሪ ዕቅድ ለማሳካት ታሳቢ በማድረግ ተጣጥሞ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

ባለፉት ስምንት አመታት በግብርና ዕድገት ፕሮግራም አንድ እና ሁለት በርካታ የግብርና ልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው÷ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም ሁለት ያልተጠናቀቁ የልማት ስራዎች በአግባቡ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ከማምረት እስከ ገበያ ድረስ በተቀናጀ መንገድ የሚሰራ ፕሮግራም መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ማጠናከያ ፕሮግራም ብሄራዊ ሥራ አስኪያጅ ከበሩ በላይነህ በበኩላቸው÷ ፕሮግራሙ ስትራቴጂክ በሆኑና በተመረጡ የግብርና ምርቶች የእሴት ሰንሰለት ተወዳደደሪነትን ማሳለጥ ፣ የገጠር ሥራ ዕድልን በመፍጠር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝግጁነትን የማጠናከር ተግባራትን በተመረጡ ወረዳዎች በማከናወን የግብርናውን ሴክተር በላቀ ደረጃ ማሻሻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.