Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየርሊጉ ቶተንሃም ፣ ቼልሲ እና  ማንቼስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ቶተንሃም ፣ ቼልሲ  ማንቸስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፏል፡፡

በምሳ ሰዓት ከሜዳው ውጭ ሉተን ታውንን የገጠመው ቶተንሃም በሚኪ ቫንዴቬን ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የአሰልጣኝ አንጌ ፖስቴኮግሉ ቡድን ቶተንሃም ነጥቡን 20 በማድረስ ፕሪሚየርሊጉን በጊዜያዊነት መምራት ጀምሯል፡፡

በሌላ በኩል ብረንትፎርድን ያስተናገደው ማንቼስተር የናይትድ ባለቀ ደቂቃ በተቆጠሩ ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

በተመሳሳይ በሁለት ጨዋታዎች መሻሻል ያሳየው ቼልሲ ከሜደው ውጭ በርንሌይን ገጥሞ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

በሌላ የ8ኛ ሳምንት መርሃግብሮች አቨርተን በርንማውዝን 3 ለ 0 እንዲሁም ፉልሃም ሼፊልድ ዩናይትድን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

በተመሳሳይ 1፡00 ላይ የተካሄደው የሀድያ ሆሳዕና እና መቻል ጨዋታ በመቻል 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የሀድያ ሆሳዕናን 2 ጎሎች ብሩክ ማርቆስ ሲያስቆጥር÷ ምንይሉ ወንድሙ (2) እና ከነዓን ማርክነህ (1) ለመቻል አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.