Fana: At a Speed of Life!

የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳኅህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች  ዓመታዊ  ስራቸውን መጀመራቸውንም ያበስራሉ፡፡

ፕሬዚዳንቷ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት የፌዴራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሐይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በፋና ቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሁሉም የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን በቀጥታ ሥርጭት እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.