Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 225 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 225 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው 5 ወንድ እና 6 ሴት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ17 እስከ 45 አመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 6 ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ፣አንድ ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ ናቸው፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ሰባቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው እንዲሁም አንደኛው ንክኪም ሆነ የውጭ ሃገር ጉዞ የሌለው ነው ብለዋል።

በዚህም አሁን ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች  ቁጥር 317 ደርሷል፡፡

እስካሁን 113 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት 197 ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ ይገኛል።

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.