Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ላይ ካሉ የአበባ እጽዋት ዝርያዎች ግማሽ ያህሉ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በዓለም ላይ ከሚገኙት 45 በመቶ የአበባ እፅዋት ላይ የመጥፋት አደጋን ተጋርጧል ሲሉ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ፡፡

በዓለም ላይ በተፈጥሮ እየደረሰ ባለው ጫና ለአደጋ ከተጋለጡት የአበባ ዕጽዋት ዝርያዎች መካከል የ’’ኦርኪድ’’ ዝርያዎች፣ የአናናስ ዝርያዎች እና ብዙ ጠቃሚ የሰብል ዝርያዎች ይገኙበታል።

ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከተገኙት 19 ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ እፅዋት እና የእንጉዳይ ዝርያዎች 77 በመቶው ለአደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉም ነው የገለጹት።

በሮያል ቦታኒክ ጋርደንስ ኬው የተካሄደው ጥናት በ30 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ 200 ሣይንቲስቶች ተገምግሟል፡፡

በሮያል ቦታኒክ ጋርደንስ ኬው ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ማቲዳ ብራውን እንዳሉት፥ ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑ እጽዋት በአየር ንብረት ለውጥና በብዝሃ ህይወት መጥፋት ስጋት ላይ ናቸው።

አክለውም፥ ከአስሩ መድሀኒቶች ዘጠኙ ከዕፅዋት እንደሚመጡ ሲታሰብ ከእፅዋት የሚገኙ መድሃኒቶችንም እንዲሁ እያጣን ነው ማለት ነው ብለዋል፡፡

የምናጣው እያንዳንዱ ዝርያ ምን አይነት እድሎችን እየነጠቀን እንደሆነም አናውቅም በማለት ገልጸው፤ ምናልባትም ካንሰርን የሚዋጋ መድሀኒት ሊሆን ይችላል ሲሉ ክስተቱ ዋጋ የሚያስከፍል እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.