Fana: At a Speed of Life!

አቶ ብናልፍ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ. ፖፕ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ግንባታ ሂደት ስለሚደግፍበት ሁኔታ መክረዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ለማቋቋም በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ለይም መወያየታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀገሪቱ የሚገኙ የቀድሞ ታጣቂዎች በሰላም ትጥቅ ፈትተው ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የሚደረገውን ሂደት ስለሚደግፉበት አግባብም መከረዋል፡፡

ለዚህም ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.