Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ ከሀይሌ ጋርመንት-ጀሞ የመንገድ ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 9፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀይሌ ጋርመንት ጀሞ እየተገነባ ያለውን መንገድ ጎብኝተዋል።

መንገዱ አዲስ አበባና አምቦ መስመርን የሚያገናኝ ነውም ነው የተባለው።

ከዚያም ባለፈ መንገዱ የአዲስ አበባ መውጪያዎችን ከኦሮሚያ አጎራባች ከተማዎች የሚያገናኙ መንገዶችን የመገንባት አንዱ ክፍል መሆኑ ተጠቁሟል።

የሀይሌ ጋርመንት —ጀሞ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቀጣይም ሁለተኛው ምእራፍ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናልም ነው የተባለው።

በመጠናቀቅ ላይ ያለው መንገድ 4ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን 6 ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ የሚችል 60 ሜትር ስፋት ያለው  መሆኑም ነው የተመላከተው።

ከዚያም ባለፈ መንገዱ የእግረኛ መጓጓዧና የብስክሌት መጓጓዧ ያካተተ ነው ተብሏል።

የመንገዱ ግንባታ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የታሰበና እንዲሁም አዲስ አበባን ከሚያዋስኑ የኦሮሚያ ከተማዎች ጋር በዘመናዊ መንገድ በማስተሳሰር የንግድ ስርአቱን ለማቀላጠፍ ያለመ  መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.