Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በኢትዮጵያ የውስጥ መፈናቀልን መከላከል የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ መፈናቀልን መከላከል የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመድ ዋና ጸሃፊ የሀገር ውስጥ መፈናቀል  ልዩ አማካሪ ሮበርት ፓይፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷አምባሳደር ምስጋኑ የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመቆጣጠር ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

መንግስት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በዘላቂነት ለመቅረፍናተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ ቀያቸው ለመመለስ የተሃድሶና መልሶ ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍም አምባሳደሩ ጠይቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ልዩ አማካሪ ሮበርት ፓይፐር በበኩላቸው ÷ የሀገር ውስጥ መፈናቀልን ለመቆጣጠር ተመድ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.