Fana: At a Speed of Life!

ቤታቸውን ሲያድሱ የነበሩ ጥንዶች የጥንት የወርቅ ሣንቲሞችን ማግኘታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የሚኖሩ ጥንዶች ቤታቸውን ሲያድሱ የጥንት የወርቅ ሣንቲሞችን ማግኘታቸው ተሰማ፡፡

የወርቅ ሣንቲሞቹ በእንግሊዝ ከ17 እስከ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደነበሩ ተነግሯል፡፡

በእንግሊዝ ሀገር ኑሯቸውን ያደረጉት ጥንዶቹ ቤታቸውን ለማደስ ባደረጉት ቁፋሮ ሲሳይ በምግብ ማብሰያ ክፍላቸው ወለል ውስጥ ተቀብሮ እየተጠባበቃቸው እንዳለ አልገመቱም ነበር፡፡

እነዚህን የወርቅ ሣንቲሞች ስብስብ በቁፋሮ ካገኙት በኋላም በለንደን የጥንት ሣንቲሞቹ ለጨረታ ቀርበዋልም ነው የተባለው፡፡

ተጫራቾቹም ፥ የ120 ዓመት የእንግሊዝ ታሪክ ወርቅ በያዘው ማሰሮ ውስጥ ተደብቆ ነበር ሲሉም ገልጸዋል።

ከፈረንጆቹ 1610 እስከ 1727 የ264 የእንግሊዝ የወርቅ ሳንቲሞች ክምችት የተገኘው በ2019 ሲሆን ፥ ስማቸው ያልተጠቀሱ ጥንዶች በተመሳሳይ የቤታቸውን የምግብ ማብሰያ ወለል ሲቆፍሩ ነው መባሉም ግጥምጥሞሹን አስገራሚ አድርጎታል።

አጫራቹ ስፒንክ እና ሶን የተባለው ድርጅት ለቢቢሲ እንዳለው ከሆነ ጨረታው የዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበ ነው፡፡

ጨረታውን ለማሸነፍም ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከቻይና እና ከጃፓን የተውጣጡ ገዢዎች እየጎረፉ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

የጨረታ አቅራቢው ግሪጎሪ ኤድመንድ ለኢንሳይደር በሰጡት መግለጫ ፥ ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ተጫራች ፍላጎት ያሳየበት ጨረታ አላየሁም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.