Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታማኝነት ብሔራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ ግብር ከፋዮች እውቅና ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 በጀት ዓመት በታማኝነት ብሔራዊ ግዴታቸውን የተወጡ ግብር ከፋዮችን ሸልመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2015 በጀት ዓመት የግብር ከፋዮች ዕውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ነው በታማኝነት ብሔራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ ግብር ከፋዮች እውቅና የሰጡት፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይም ባስተላለፉት መልእክት ÷ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና ማኅበረሰቡ የገቢ መሰረትን የሚያሳድጉ ስራዎችን እንዲደግፉ አሳስበዋል፡፡

ሌብነትን፣ ኮንትሮባንድ እና ሕገ ወጥነትን ማስወገድ፣ ስርዓትን እና ተገማችነትን ማካተት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

መንግስት የግብር አከፋፈል ስርዓቱን እና አሰራሩን ማዘመን ሲኖርበት፣ የግሉ ዘርፍም መሳ ለመሳ በቴክኖሎጂ መዘመን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ጥቅል የገቢ እቅድ 450 ቢሊየን የነበረ ሲሆን ፥ ክንውኑ 442 ቢሊየን ሆኖ ተጠናቋል።

ከዚህ ውስጥ በበጀት ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ግብር የተሰበሰበው 264 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር ነበር።

በዛሬው መርሐ ግብር ላይ በአጠቀላይ 500 ግብር ከፋዮች እውቅና እንደተሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.