Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በአፈፃፀምና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ተቋማቱ ተልዕኳቸውን መሰረት በማድረግ ሀገሪቷ ያለባትን ጫና በመሸከም ሀገርና ህዝብን ከአደጋ ለመከላከል እያደረጉ ያለው ርብርብ ውጤታማ እንደሆነ ተገምግሟል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ከሚጠበቅባቸው ዘርፈ ብዙ የሀገርና ህዝብ ኃላፊነት አንፃርም በርካታ ቀጣይ የቤት ሥራዎች እንዳሉም ተመልክቷል፡፡

ለዚህም በጋራ እና በተናጠል የበለጠ ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ሚኒሰትሯ ማሳሰባቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.