Fana: At a Speed of Life!

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የታየውን ውጤት ለመቀየር ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና ይጠናከራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ለመቅረፍ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንደሚጠናከር የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በአገልግሎቱ የፈተና አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ወንደሰን ኢየሱስወርቅ ለውጤት መቀነስ አንዱ ምክንያት ተማሪዎች በታችኞቹ የትምህርት ደረጃዎች በተገቢው ፈተና እየወሰዱ አለመምጣታቸው ነው ብለዋል።

ይህም ተማሪዎች በየደረጃው ማወቅ ያለባቸውን እንዳያውቁ ማድረጉን ገልጸው፤ በስተመጨረሻ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ተማሪዎች በተገቢው ምዘና እንዲያልፉ ይደረጋል በማለት ገልጸው፤ ይህንንም ለመተግበር በ8ኛ ክፍል የሚሰጠውን ፈተና ከማጠናከር ባለፈ በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ምዘና ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉን አቀፍ የማሻሻል ስራዎች እንደሚያስፈልግ የፈተናዎች ስራ አስፈፃሚ ወንድወሰን ኢየሱስ ወርቅ ተናግረዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.