Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በትብብር ለመስራት ተስማሙ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመሆን ለሚያሰራው የመረጃ ዌብ ፖርታል ስምምነቱን የፈረሙት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ÷ተቋሙ አሁን ያለውን የዲጂታል ዓለም ፍጥነት ያገናዘበ የመንግስት የመረጃ ፍሰትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመሆን የሚያሰራው የመረጃ ዌብ ፖርታል የሃገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃንና ማንኛውም መረጃ ፈላጊ በሙሉ የመንግስትን እቅዶች፣ ፖሊሲዎችና ተግባራትን የተመለከቱ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የሚያስችል እንደሚሆን ተገልጿል።

ከአገልግሎቱ መረጃዎች ባሻገር የፌዴራልና የክልል ኮሙኒኬሽን ተቋማት መረጃዎቻቸውን ለሕዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበትን አሰራርማካተቱም ተጠቁሟል፡፡

የኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ በበኩላቸው÷ አዲስ የሚለማው ዌብ ፖርታል ለመረጃ ፈላጊዎች በቀላሉ መገኘት እንዲችል፣ ለአጠቃቀም ምቹ እንዲሆንና በውስጡም የተለያዩ የመረጃ አማራጮችን እንዲይዝ ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም ዜጎች በተለያዩ የመንግስትና የክልል የቋማት ላይ ያላቸውን ጥያቄ፣ አስተያየትና ቅሬታ የሚያቀርቡበትን አሰራር የያዘ መሆኑ በስምምነቱ ወቅት መገለፁን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዌብ ፖርታል በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ስራው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.