Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም ባንክና ከአይኤምኤፍ አመራሮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ ማራኬሽ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ እና ከአለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫጋር ተወያየ።

ልዑኩ በሞሮኮ ማራኬሽ በሚካሄደው የዓለም ባንክ ግሩፕ አይኤምኤፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ይሳተፋል።

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ባካሄደው ውይይት ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም የዓለም ባንክና የአይኤምኤፍ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የልማት ስራዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

የማክሮ ፊስካል መረጋጋት፣ የግሉ ዘርፍ ልማት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ መልሶ ግንባታና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ሁለቱም ተቋማት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን ለማስተካከል እንዲሁም በሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየወሰደች ያለውን የለውጥ እርምጃ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ላይ አቅዳ እየሰራች ያለውን ግብ ለማሳካት ተቋማቱ መደገፍ ስለሚችሉበት ሁኔታ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.