Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 20 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 20 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ።

ታጣቂ ቡድኑ ትናንት ጠዋት በሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ባደረሰው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ ከ14 የሚበልጡ ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው።

በጥቃቱም ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ሰለባ እንደሆኑም ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ወደ መንደሩ ከደረሱ በኋላ ጥቃት አድራሾቹ የሸሹ ሲሆን በኋላ ላይ ታጣቂዎቹ በተባበሩት መንግስታት ጣቢያ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ታውቋል።

በሃገሪቱ በሁለት ወራት ውስጥ በጎሳ ግጭት 200 ሺህ ሰዎች ከቤት ከንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.