Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ለኢትዮጵያ የ4 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ ለኢትዮጵያ የ4 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉ በኢትዮጵያ በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለሚተገበረው የስነ ንጽህና መጠበቂያ ፕሮግራም እንደሚውል በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሄሌና ኤራክሲነን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚያግዝ መልኩ የውሃ አቅርቦትን ማዳረስ፣ ስነ ንጽህናን ማረጋገጥ እንዲሁም የፍሳሽ አወጋገድን ማሻሻልም የድጋፉ አካል ነው ተብሏል።

አምባሳደሯ ፊንላንድ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።

#fbc

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.