Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 775 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 17 ወንዶች ሲሆኑ 18ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው፤ እድሜያቸውም ከ15 እስከ 80 ድረስ ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆን አንደኛው የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ 23ቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

አምስቱ ደግሞ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ አራት ሰዎች ደግሞ ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ እንዲሁም አንድ ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ ናቸው።

ተጨማሪ 3 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው የተባለው።

ሚኒስትሯ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች ውስጥ ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰጠ መግለጫ በኮቪድ19 ምክንያት ህይወታቸው ካለፈው የ75 አዛውንት ግለሰብ ጋር ንክኪ አላቸው በሚል 25 ሰዎች ተለይተው ክትትል ሲደረግላቸው ከቆየ በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ 5 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መገለጹን አስታውሰዋል።

በዛሬው እለት ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥም 22ቱ በወቅቱ ከተጠቀሱት አምስት ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውና ክትትል ላይ ከነበሩ 94 ግለሰቦች መካከል እንደሆኑም አስረድተዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.