Fana: At a Speed of Life!

ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የነፃነት፣ የጽናት፣ ሀገርን የመውደድና የአልበገር ባይነት መገለጫ ነው – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የነፃነት፣ የጽናት፣ ሀገርን የመውደድና የአልበገር ባይነት መገለጫ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ተናገሩ።

16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ተከበረ።

ቀኑ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ኃሳብ ተከበረ ።

በመርኃ-ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የሠራዊቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንዲሁም ሲቪል ሠራተኞች ታድመዋል።

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ÷ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የነፃነት፣ የጽናት፣ ሀገርን የመውደድና የአልበገር ባይነት መገለጫ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ሰንደቅ ዓላማ ከሠራዊቱ ጋር የተለየ ትስስር ያለው መሆኑን አንስተው፤ ሠራዊቱ ሁሌም ሰንደቁን ከፊት በማስቀደም ሀገርን እያሰበ የሚኖር ሠራዊት ነው ብለዋል።

ለመላው የሠራዊቱ አባላትም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.