Fana: At a Speed of Life!

በህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ላይ የባለሙያዎችን ሃሳብ ለመስማት የተዘጋጀው መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ላይ የባለሙያዎችን ሃሳብ ለመስማት የተዘጋጀው መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ ባለፈው ቅዳሜ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የህገ መንግስት ትርጉምን በተመለከተ ያዘጋጀው የባለሙያዎች ሀሳብ መስጫ መድረክ ቀጣይ ክፍል ነው።

በውይይቱ ላይ በባለሙያዎች የቀረቡ ጽሑፎች እየተመረመሩ መሆኑን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሰብሳቢ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ህገ መንግስቱ ሲረቀቅ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምሁራን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

ከዚህ ባለፈም በሽግግር መንግሥት ወቅት በተለያዩ ሃላፊነት የሰሩ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የህግ ባለሙያዎች ሃሳባቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የባለሙያዎቹ አስተያየት መስጫ መድረክ ጉባኤው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረበለት ጥያቄ የሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለሙያዎች አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥሪ ባደረገው መሰረት ነው እየተካሄደ ያለው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.