Fana: At a Speed of Life!

ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 9 ወራት ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስትሩ በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 68 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 2 ቢሊየን 900 ሺህ ዶላር ማግኘቱን አስታውቋል።

አፈፃጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ ጭማሪ እንዳለውም ገልጿል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም ላይ የንግድ ግንኙነት የተቀዛቀዘ ቢሆንም ኢትዮጵያ እያመረተች ያለው ለምግብነት የሚውሉ ምርቶች በመሆናቸው ገቢው ሊጨምር መቻሉን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ጫት በዘጠኝ ወራት ከተያዘላቸው እቅድ በላይ አፈፃጸም ያስመዘገቡ ሲሆን የብዕርና አገዳ እህሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ ቡና፣ ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት የእቅዳቸውን 75 በመቶ አፈጻጸም አሳይተዋልም ነው ያሉት።

እንዲሁም ታንታለም፣ የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ስጋ፣ ቅመማ ቅመም፣ ባህር ዛፍ እና ሻይ ቅጠል የእቅዳቸውን ከ50 እስከ 74 በመቶ ገቢ ማስገኘታቸውን ጠቅሰዋል።

በአንፃሩ ወርቅ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንስሳት የእቅዳቸውን ከ50 በመቶ በታች አስመዝግበዋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.