Fana: At a Speed of Life!

የአማዞን ወንዝ በመቶ ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ግዙፍ ደን እምብርት የሆነው የአማዞን ወንዝ በመቶ ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የውሃ መጠኑ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

የዘመኑን ክብረ ወሰን የሰበረው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ኑሮ ያመሰቃቀለ እና የአካባቢውን ሥነ-ምህዳርም የጎዳ መሆኑ ተመላክቷል።

በፍጥነት እየደረቁ ያሉ የአማዞን ገባር ወንዞችም የውሃ መጠናቸው በመቀነሱ ጀልባዎች እንዲቆሙ በማድረግ በርቀት ላይ ለሚገኙ መንደሮች የሚደረገውን የምግብ እና የውሃ አቅርቦት ለመቋረጥ መገደዱ ተጠቁሟል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በተከሰተው ከፍተኛ የውሃ ሙቀትም ሊጠፋ በተቃረበው ወንዝ ውስጥ ከ100 በላይ ዶልፊኖች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተመላክቷል።

በሪዮ ኔግሮ እና በአማዞን ወንዝ ዙሪያ በተካሄደው ስብሰባ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያለው የማኑስ ወደብ ከተማ አሁን ላይ 13 ነጥብ 59 ሜትር ውሃ እንደተመዘገበበት እና ከዓመት በፊት 17 ነጥብ 60 ሜትር እንደነበር ተነስቷል።

ይህም በፈረንጆቹ 1902 ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ ዝቅተኛው ደረጃ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2010 በዝቅተኝነት የተመዘገበውን መጠን ማለፉንም ኤዢያ ዋን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.