Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንና በመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መካከል የቴክኖሎጂ አቅርቦት የማእቀፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና በመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መካከል ባለስልጣኑ የጀመራቸውን የብቃት ሞዴል ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዙ የቴክኖሎጂ አቅርቦት የማእቀፍ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሰው ሃይል አቅም በተለይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ነው ተብሏል።

በዚህም የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ድጋፍ ማድረግ የሚቻልባቸው ዘርፎችን በመለየት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ያግዛል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ስምምነቱ ተቋሙን የማዘመን አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግና ብክነትና መሰል የአገልግሎት አሰጣጥ መሰናክሎችን በዘመናዊ መልኩ ለመተካት የሚረዳ ነው ብለዋል።

የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ግንኙነት ውጤታማና ተመጋጋቢ ለመሆን ይችል ዘንድ ፕሮጀክቱን በተባለው የጊዜ ገደብ ለመፈፀም ተቋማቸው እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ኤጀንሲው ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ የትብብር ስምምነቱ ዘላቂ ሀገራዊ ስራዎችን ለመከወን ይረዳል ማለታቸውንም ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.