Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡና ተወዳጅነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት መስራት ይገባል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ላይ ያለው ተወዳጅነትና ተመራጭነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።

በቡና ወጪ ንግድ እየተመዘገበ ባለው አመርቂ ውጤት መዘናጋት ሳይፈጠር ይበልጥ መሥራት እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ ካላት ምቹ የዓየር ንብረት፣ ሰፊ መሬት እንዲሁም የሰው ኃይል አንጻር በርካታ ዕድሎች አሏትም ብለዋል፡፡

በዘርፉ እየተከተልን ካለው የተለመደ አሠራር ወጣ ብለን ማሰብ ይገባናልም ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

በቴክኖሎጂ የተደገፉ ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ የሀገር ውስጥ ገቢ ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ተግዳሮቶችን ወደጥሩ አጋጣሚ መለወጥ÷ በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ተግባር እንደሆነም ማስገንዘባቸውን ከቡናና ሻይ ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.