Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተሠሩ ስራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቢሾፍቱ በመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተሠሩ ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝታቸውም የሞተር ቬሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተከናወኑ የፈጠራ፣ የምርምር ውጤቶችን እና ምርቶችን ተመልክተዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እንደ አዲስ ከተደራጀበት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ነባር እና አዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመያዝ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማምረት እና የማዘመን ስራ እንደሚያከናውን ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የቀላል እና የመካከለኛ መሣሪያ ተተኳሾችን እንዲሁም እስከ 122 ሚሊ ሜትር ድረስ ያሉ የሮኬት ተተኳሾችን እንደሚያምርት ተገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ BRDM-2 ፣ PTR -60ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን፣ T-55 እና T-72 ታንኮችን የመጠገን፣ የማደስ እና ማሻሻያ የማድረግ አቅም የገነባ ሲሆን በተጨማሪም የመከላከያ ሠራዊቱን የማድረግ አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን ያከናውናል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን አውደ ርዕይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ማስጀመራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.