Fana: At a Speed of Life!

አካል-ጉዳተኞችን ያማከለ የትምህርት መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አካል ጉዳተኞችን ያማከለ የትምህርት መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ፡፡

“ላይት ፎር ዘ ወርልድ” የተሰኘው በጉዳዩ ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኤርጎጌ ተሥፋዬ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግርም፤ ትምህርትን ለሁሉም እኩል ማድረስ ይቻል ዘንድ አካል ጉዳተኞችን አካታች ፖሊሲ ማዘጋጀት አሥፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

ሚኒስቴሩ ለአካል ጉዳተኞች የትምህርት ሁኔታ ትኩረት በመሥጠትም ጉዳዩ በመንግሥት ደረጃ እንዲታይ መስራቱን ነው የተናገሩት፡፡

የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት እና ለተለያዩ ጉዳዮች ምላሽ የሚሠጥ ቢሮ በሚኒስቴሩ መቋቋሙንም ጭምር ነው የገለጹት።

የአካል ጉዳተኞች ሕግ ለመቅረፅም ሚኒስቴሩ ከምግባረ-ሠናይ ድርጅቶች እና ማኅበራት ጋር በመተባበር በመሪነት እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የ”ላይት ፎር ዘ ወርልድ” ተወካይ የሆኑት ዐይናለም ተፈራ በበኩላቸው÷ መርሐ-ግብሩ አካል ጉዳተኞች በማኅበረሰቡ ውስጥ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል ማለታቸውን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.