Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ለትምህርት ቤቶች ግንባታ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ለትምህርት ቤቶች ግንባታ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ነው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተመራ ቡድን በአዳማ የሚገኙ መዋዕለ ህጻናትን (ቡኡራ ቦሩ) የትምህርት እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ ባሪሶ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ቶላ ባሪሶ (ዶ/ር) ባለፈው ክረምት በትምህርት ቤቶች ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸው፤ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን ተናግረዋል።

የቡኡራ ቦሩ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ህጻናትን በማስተማር ብዙ ውጤት ማስገኘቱንም ተናግረዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የጠቀሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በበኩላቸው የትምህርት ውድቀትን ለመቅረፍ ለትምህርት ቤቶች የተሰጠው ትኩረት አበረታች ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ለትምህርት ቤቶች ግንባታ የተሰጠው ትኩረትና የተፈጸመው ተግባርም በምሳሌነት እንደሚጠቀስ ተናግረዋል።
በበኃይሉ ባኔ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.