Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ኮርያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮርያ ጥምረት የተገነባው የኢትዮ ኮርያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ተመረቀ፡፡

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተካሄደው የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የኢንዱትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ÷  እንደ ሀገር ከፍተኛ አምራች ኃይል እና የገበያ ፍላጎት መኖር፣በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎች አለመኖር እንዲሁም የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ የአፍሪካን ገበያ ሰብሮ ለመግባት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በግብርና አምራች ኢንዱስትሪ ያሉ እምቅ ሃብቶች በግብርና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለመሰማራት ምቹ ያደርጋታል  ሲሉ መናገራቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቴክኖሎጂ፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ፣ በሃይል (ኢነርጂ) እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ የተካኑ የደቡብ ኮርያ ባለሙያዎች የኢትዮጵያን ኢንዱስትርያላይዜሽን ሊደግፉ ይችላሉ ያሉት አቶ ሃሰን በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የቴክኖሎጂ ሽግግር ፣አቅም ግንባታ እና የእውቀት ሽግግርን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ከኢኮኖሚዊ ትስስር ባለፈ በሁለቱ አገራት መካከል የትምህርት፣ የባህል እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወዳጅነትን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሃሰን በቀጣይም የሁለቱን አገራት ትስስር የሚያበረታታ እና የሚያጠናክር ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ አገራት የጋራ ጥምረት የተገነባው ይህ ፓርክ በርካታ አገልግሎት የሚሰጥ እና በዋናነትም በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ የስልጠና እና የላብራቶሪ አገልግሎት እንዲሁም አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦች ማመንጫ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገልግል ተግልጿል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.