Fana: At a Speed of Life!

“የተቃጡብንን ወረራዎች በጀግኖች አኩሪ ገድል በድል ተወጥተናል”- ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተቃጡብንን ወረራዎች በጀግኖች አኩሪ ገድል በአሸናፊነት ተወጥተናል ሲሉ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ፡፡

116ኛውን የኢትዮጵያ ሠራዊት ቀን የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ከጋምቤላ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።

የዕዙ ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ÷ቀኑ ሠራዊቱ ከቀደምቶቹ የወረሰውን ጀግንነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ የሚተጋ የኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያ መከታ መሆኑ የሚታወስበት ነው ።

ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪ ኃይሎችና ከፀረ ሰላም ሃይሎች በመከላከል የሀገራችን ሰላም እንዲጠበቅ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲቀጥል ማድረግ የሰራዊቱ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተቃጡብንን ወረራዎች በጀግኖች አኩሪ ገድል በድል ተወጥተናል ማለታቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው÷ሠራዊቱ የኢትዮጵያ ህዝብ አለኝታና በመስዋዕትነት ሀገር ያፀና ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ቀን ስናከብር ሀገራችን ታፍራና ተከብራ እንድትኖር መስዋዕትነት የከፈለ ሠራዊትን በማሰብ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

ሰላማችን በአስተማማኝ መሰረት እንዲቆም፣ ልማት እንዲቀጥል እና የህዳሴ ጉዞ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል የሰራዊቱ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.