Fana: At a Speed of Life!

የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የሀገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል፡፡

በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል÷ የሀገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት አጠቃላይ ከተሰጡ ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50 በመቶ) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል ያገኙ ተፈታኞች ብቻ መማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ውጤቱንም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/…/Apply ForAdmis…/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስምና የይለፍ ቃል በመጠቀም ማረጋገጥ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.