Fana: At a Speed of Life!

የፓኪስታን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሀገርን ሚስጠራዊ ህግ በመጣስ ወንጀል ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ ሙሀመድ ኩሬሺ የሀገርን ሚስጠራዊ ህግ በመጣስ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የፓኪስታን ልዩ ፍርድ ቤት ዳኛ ሀስናት ዙልቃርኒያን÷ የቀድሞ ባለስልጣናቱ ላይ የቀረበው ክስ መረጃ መደበቅ በመባል እንደሚጠራ ገልጸዋል።

ባለስልጣናቱ ከህዝብ እውቅና ውጭ ከሌሎች ሀገራት ጋር መረጃ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተመሰረተ ነው ብለዋል፡፡

ኢምራን ካሃን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት አምባሳደሮቻቸው ከሁለት ከፍተኛ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ጋር ከተገናኙ በኋላ የተለዋወጡት ሚስጥራዊ የዲፕሎማሲያዊ ዶክመንት ለክሱ መነሻ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ የኢምራን ካሃን ረዳት በነበሩት መሐመድ አዛም፣ የቀድሞ የፓኪስታን ፌደራል ሚኒስትር በነበሩት አሳድ ኡመር እና ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ምንጮች እንደሚገልፁት ኢምራን ካሃን በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ አቋም ከመያዛቸው በተጨማሪ በሞስኮ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ አሜሪካ በኢስላማባድ ላይ ባደረገችው ጣልቃ ገብነት ስልጣናቸውን አጥተዋል፡፡

ዋሽንግተን በበኩሏ በወታደራዊ ሀይል በስልጣን ከተወገዱት ኢምራን ካሃን ጀርባ እጇ እንደሌለበት መናገሯን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.