Fana: At a Speed of Life!

ከሰዓት በኋላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ – ጥናት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰዓት በኋላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች በአንጻራዊነት ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ሲል አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

ጥናቱ በዚህ ዓመት 18 በናቹራል ኮሙኒኬሽን እትሙ በብሪታኒያ ባዮሜዲካል ዳታቤዝ ውስጥ ከ92 ሺህ ሰዎች የጤና እና የስነ-ሕዝብ መረጃን ገምግሟል።

በዚህም እኩለ ቀን ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች በምሽት እና በጠዋቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር በአጠቃላይም ሆነ በልብ በሽታ የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው።

ከሰዓት በኋላ የሚሰራ ወጥ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካንሰርን ጨምሮ በተለያዩ ከልብ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የመሞት እድልን ይቀንሳል መባሉን ኢንሳይደር በዘገባው አመላክቷል፡፡

ባለፈው ዓመት በተደረገ ጥናት የጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሴቶች የሆድ ድርቀት እና የደም ግፊትን እንዲቀንሱ የሚረዳ ነው ያለ ሲሆን፥ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የጡንቻ ጥንካሬ እና ጥሩ ስሜት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋልም ነው የተባለው።

ለዓይነት 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭ የሆኑ 32 ወንዶችን አካትቶ በፈረንጆቹ 2020 የተደረገ ጥናት ከሰዓት በኋላ የሚደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በተሻለ ሁኔታ እንዲቆጣጠር መርዳቱን አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ሊያሻሽል እና ያልተገባ ኮሌስትሮልን ጠዋት ከሚደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በተሻለ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል ሲል በፈረንጆቹ 2021 የተደረገ አንድ ጥናት ጠቁሟል።

ሆኖም በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፥ ምንም ጊዜ ቢሆን የሚከወን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የከባድ በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ፣ ጥሩ ስሜት ለመፍጠር፣ የደም ግፊትን ለመቀነስ፣ ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስና በአጠቃላይ ረዘም ላለ ጊዜ ለመኖር አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.