Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ ቀንን እያከበረ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ 116ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ምስረታ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።

በዓሉ “በተፈተነ ጊዜ የሚፀና የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በሐረር ከተማ በሚገኘው መኮንኖች ክበብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድበት ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በበዓሉ ላይ የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ፣ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም የሐረሪ ክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.