Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከኢትዮ-ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከኢትዮ-ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቤቲ ዙ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኮሚቴው ከተቋቋመ ጊዜ  ጀምሮ እስካሁን ባስመዘገባቸው ውጤቶች እንዲሁም በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርቦ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ተፈራ ደርበው÷ ኮሚቴው እያከናወኑ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በፊት በቤጂንግና ሻንግሃይ ለተካሄዱ የኢንቨስትመንት ፎረሞችም ኮሚቴው ያደረገውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ ትኩረት በምታደርግባቸው ዘርፎች እንደ ማዕድን፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝም፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ኢነርጂ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እንዲሁም የአይ ሲ ቲ ዘርፎች ላይ በማተኮር ኮሚቴው እንዲሰራም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቤቲ ዙ በበኩላቸው÷ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመጥቀስ በዋናነት “ላይት አፕ ኢትዮጵያን ቪሌጅ“በሚል ስያሜ ኮሚቴው እያከናወነ ስላለው ፕሮጀክትም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ኮሚቴው በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት እድሎች ለቻይና ባለሀብቶች በማስተዋወቅ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በዚሀም ከ300 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች፣ ንግድ ምክር ቤቶች እና ማህበራት ተቀራርበው እንዲሰሩ እያደረገ ነው ማለታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.