Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካዔል የቻይናን የሕዝብ ደኅንነት ልዑካን ቡድን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካዔል በቻይና የሕዝብ ደኅንነት ምክትል ሚኒስትር ዡ ዳቶንግ የተመራውን ልዑካን ቡድን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ÷ የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ ፖሊስ በተለያዩ የሙያ መሥኮች የትምህርት እና ሥልጠና ዕድል እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውሰው አመሥግነዋል፡፡

አያይዘዉም የቻይና ባለሐብቶች በኢትዮጵያ በተሰማሩባቸው የልማት ሥራዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ፖሊስ አሥፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት እና የተለያዩ ዓለምአቀፍ ዲፕሎማት መቀመጫ እንደመሆኗም ፀጥታዋ አስተማማኝ ሊሆን የቻለው ፖሊስ ፣ የጸጥታ አካላት እና ሕዝብ ተባብረው በመሥራታቸው ነው ብለዋል።

የቻይና ሕዝብ ደኅንነት ምክትል ሚኒስትር ዡ ዳቶንግ በበኩላቸው ÷ የቻይና የልማት ፕሮጀክቶች ደኅንነት እንዲጠበቅ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ተቀራርበው መረጃ በመለዋወጥ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ተግባራትን ጎብኝተው የፖሊስን ተቋም ለማዘመን እየተሠሩ ላሉት ሥራዎች አድናቆታቸውን መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.