Fana: At a Speed of Life!

በግብርና ሥራ ፈጠራ ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ትራንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በግብርና ሥራ ፈጠራ ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል፡፡

በግብርና ሥራ ፈጠራ ላይ ትኩረት ያደርጋል በተባለው“ኤ ዲ ኢ ዋይ” ፕሮግራም 80 በመቶ ተጠቃሚዎች ወጣት ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ ለአምስት አመታት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵየ እና በሶማሌ ክልሎች ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ 74 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የሚተገበር መሆኑን ተገልጿል፡፡

“ኤ ዲ ኢ ዋይ” ወጣቶችን በግብርና ግብዓቶችና ግብይት፣ በእሴት ጭመራና በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ የሥራ እድል የሚፈጥር ፕሮግራም እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

“ኤ ዲ ኢ ዋይ” ለ611 ሺህ 343 ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር እንዳለመ የተገለጸ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 427 ሺህ 940 በግል ሥራ የሚተዳደሩ እንዲሁም 183 ሺህ 403 ደመወዝተኛ ወጣቶችን የእድሉ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር)÷ፕሮግራሙ የሥራ እድል ከመፍጠር ባሻገር በወጣት ሴቶች ህይወት ላይ በጎ ተጽእኖ በመፍጠር ተጨማሪ አቅም እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሳሙኤል ያለው አዴላ በበኩላቸው÷ “ኤ ዲ ኢ ዋይ” ወጣቶች የክህሎትና የቴክኖሎጂ እውቀት እንዲያገኙ ያስችላል ማለታቸውን የግብርና ትራንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.