Fana: At a Speed of Life!

ሳንድሮ ቶናሊ ለ10 ወራት ከእግርኳስ ታገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኒውካስል ዩናይትዱ የመሀል ክፍል ተጫዋች ሳንድሮ ቶናሊ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ለ10 ወራት ከእግርኳስ መታገዱን የጣሊያን እግኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ወጣቱ ጣሊያናዊ ኤሲ ሚላን በነበረበት ወቅት ህገ ወጥ የእግርኳስ ደህረ ገፆችን በመጠቀም የእግር ኳስ ውርርድ ማድረጉ በመረጋገጡ ነው ውሳኔው የተላለፈበት፡፡

ውሳኔውን ተክትሎም ቶናሊ በቀሪ የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታዎች ለኒውካስትል አገልገሎት የማይሰጥ ሲሆን በኢሮ 2024 የማጣሪያ ጨዋታዎች ለጣሊያን ብሄራዊ ቡደን ሊስለፍ እንደማይችል ተረጋግጧል፡፡

የ23 ዓመቱ የመሀል ክፍል ተከላካይ እስከ ነሀሴ 2024 ምንም አይነት አለማቀፋዊ ጨዋታዎችን እንዳይጫዎት የታገደ ሲሆን ኒውካስትል ዩናይትድ በሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ግን መሳተፍ ይችላል ተብሏል፡፡

በፈፋ ህግ መሰረት ጉዳዩ እስከ ሶስት አመታት ከእግርኳስ ሊያሳግድ ቢችልም ቶናሊ በማጣራት ሂደቱ ያሳየው ተባባሪነት የቅጣት ውሳኔው እንዲቀልለት አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ቶናሊ ከቁማር ሱሱ እንዲያገገም የስነ ልቦና ህክምናውን መከታተል እንዳለበት እና ከጣሊያን እግኳስ ፌደሬሽን ባለስልጣናት ጋር ቆይታውን በተመለከተ በቅርበት እንዲነጋገር ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.