Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ሉዓላዊነትና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን – የሠራዊቱ አባላት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተናገሩ፡፡

116ኛው የሠራዊት ቀን “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚጸና የድል ሠራዊት”በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡

በአከባበር ሥነ -ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሠራዊቱ አባላት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ በቀደምት ጀግኖች አባቶች ጽኑ ተጋድሎ ለየትኛውም ሃይል ሳትንበረከክ ቆይታለች፡፡

እኛም ሉዓላዊት እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ በክብር ለማስተላለፍ በቁርጠኝነት እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ለሕገ መንግስቱ ታማኝ በመሆን ከራስ በፊት ለሀገርና ሕዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት የማንም ወገንተኝነት እንደሌለው የገለጹት አባላቱ÷ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አስፈላጊውን ወታደራዊ ስብዕና ተላብሰው እንደሚሰሩ አንስተዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

መከላከያ ሠራዊት የሀገርን አንድነት ለማጽናት ለከፈለው እና እየከፈለ ለሚገኘው መስዋዕተነት እውቅና መስጠት ለቀጣይ ተልዕኮ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፤ የሠራዊት ቀን በደመቀ ሁኔታ መከበሩ የደስታ ሥሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.