Fana: At a Speed of Life!

ከሙከጡሪ-ኮከብ መስክ የመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሙከጡሪ-ኮከብ መስክ የመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ በጥሩ ሁኔታ ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

58 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነውን የሙከጡሪ-ኮከብ መስክ ፕሮጀክት የመስክ ቅኝት ተካሂዶል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ በወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች ሳቢያ በእቅዱ መሰረት ለመስራት ሲቸገር ቆይቷል።

በአሁኑ ወቀት ያሉት ዋና ዋና ችግሮች በመቀረፍቸው ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ መሆኑን ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቀት 12 ኪሎ ሜትር የአስፖልት ማንጠፍ ስራ የተሰራ ሲሆን እስከ ተያዘው አመት መጨረሻ ድረስም ከ20 ኪሎሜትር በላይ ለማከናወን በትኩረት እየተሰራ ነው።
አጠቃላይ ፕሮጀክቱን በቀጣይ አመት ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተበሎ ይጠበቃ።

ይህ እንዲሆን አሁንም ከወሰን ማሰከበር ጋር ተያይዞ ያልተፈቱ ችግሮችን ለማቃለል የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለፀው።

የሙከጡሪ -ኮከብ መስክ መንገድ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲገነባ ሆኗል።

768 ሚሊየን 622 ሺህ ብር እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለመስመሩ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍይዳዎችን እንዳሉ ተነግሯል።

በመንገዱ የሚዋሰኑ የኦሮሚያና የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቀላሉና በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደ ተላያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለማመላለስ ያስላቸዋል ተብሏል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.