Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች የተከናወኑበት የሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በአዳማ ማካሄድ ጀመረ።

ዛሬ በጀመረው የአፈጻጸም ግምገማ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በተጀመረው ግምገማ 2016 ዓ.ም እንደ ፓርቲና መንግስት የታቀዱ ስራዎች ምን ያህል ተግባራዊ ሆነዋል የሚለውን በስፋት እናያለን ብለዋል።

አያይዘውም ዕቅዶቹ ምን ያህል በብዛት፣ በጥራትና በፍጥነት ተከናውነዋል የሚለው የሚታይበት እንደሆነም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ባለፉት ሶስት ወራት በፓርቲ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን እንደ መንግስት ደግሞ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.