Fana: At a Speed of Life!

ለምክር ቤት አባላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና መሰጠት ጀመረ።

ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚቆይ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

በስልጠና ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና አባላት ተገኝተዋል።

በስልጠናው ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም፣ የልማትና ሌሎች ጉዳዮችን መነሻ ያደረጉ ፅሑፎች ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.