Fana: At a Speed of Life!

ኢንዲስትሪዎች የሀገር ውስጥ የገበያ አማራጮችን እንዲጠቀሙና የኮቪድ-19 መከላከያ መሳሪያዎችን ማምረት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮቪድ-19 ተፅኖ ምላሽና በኢንዲስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት አምራች ድርጅቶች ባጋጠማቸው ችግሮች ዙሪያ የቪዲዮ ገፅ ለገፅ ውይይት ተካሄደ።
 
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር የኮቪድ-19 ተፅዕኖ እና ቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ ነው ውይይት ያካሄዱት።
 
በውይይቱ በኢንዲስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት አምራች ድርጅቶች በሀገር ውስጥ ሌሎች የገበያ አማራጮችን እንዲጠቀሙ፣ የኮቪድ 19 መከላከያ መሳሪያዎችን ማምረት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እና የውጭ ሀገር የገበያ ዕድሎችን አሟጠው እንዲጠቀሙ የጋራ አቅጣጫዎች ተቀምጧል።
 
የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ኃላፊ ሌሊሴ ነሚን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.