Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነርን አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር በጽህፈት ቤታቸው ተቀበለው አሰናበቱ።
 
አቶ ገዱ አምባሳደሯ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያንና የጀርመንን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
 
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዓለም ላይ በደረሰው የሰው ህይወት ህልፈት ሃዘናቸውን የገለጹት ክቡር አቶ ገዱ፤ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለምታደርገው ጥረት ጀርመን እያደረገች ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጠሉ አቶ ገዱ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
 
ኢትዮጵያ በቀጠናው እያደረገች ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከታላቁ የአትየጵያ ህዳሴ ግድብ ግንበታ ጋር በተያያዘ እስከ ዛሬ ያደረጉትን ውይይት በተመለከተም ገለጸ አድርገዋል።
 
አምባሳደር ብሪታ ዋግነር በበኩላቸው በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውንና በኢትዮጵያ መንግስት ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
 
ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
 
 
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ትብብር የሚያሻው በመሆኑ፤ ጀርመን በሽታውን ለመቋቋም ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናከራ እንደምትቀጥልም አምባሳደሯ አንስተዋል።
 
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.