Fana: At a Speed of Life!

በእንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የሽሮሜዳ አካባቢ ጣቢያ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የጣቢያው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቅሩ ማሞ እንደገለጹት÷ ዮናስ ዳኜና ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሩ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በፓርኩ ዙሪያ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ የኃይል ተግባር በመጠቀም የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል በመፈፀም ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን ሲዘርፉ ቆይተዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡ እና የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቅረታቸውንም አመላክተዋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች በተደጋጋሚ ቀጠሮ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው በሌሉበት እያንዳንዳቸው በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል፡፡

ፖሊስም ፍርደኞቹን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት ለማስረከብ ባደረገው ጥረት ዮናስ ዳኜ የተባለው ግለሰብ ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉ እና ግብረአበሩን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በእንጦጦ ፓርክ ለመዝናናት የሚመጡ ግለሰቦችም የደኅንነት ስጋት እንዳይሰማቸው ፖሊስ የመከላከል አቅሙን በማሣደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ እና ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎችን ማስቆም መቻሉንም አረጋግጠዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.